info@bongau.edu.et.com     0474524523     0474524510  

Social Activities

Odoo • Image and Text

ሚያዝያ 28, 2011 ዓ/ም

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለጌዲኦ ዞን ተፈናቃዮች ሁለተኛ ዙር ድጋፍ አደረገ፤

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሆኑት በክብርት ሚኒስቴር ፕ/ር ሂሩት ወ/ማርያም በተደረገው ጥሪ መሠረት ለተፈናቃዮቹ 300 የቤት ክዳን ቆርቆሮ እና 200 ኩንታል የጤፍ፣ የሽሮ እና የበርበሬ ዱቄት በመጫን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና ም/ፕሬዝዳንቶች ተወካዮችን በቀን 27/08/2011 ዓ/ም ወደ ስፍራው የሸኙአቸው ሲሆን በተመሳሳይ መልኩም በ2010 ዓ/ም ችግሩ በተከሰተበት ወቅት ዩኒቨርሲቲው ለተፈናቃዮቹ “ለወገን ደራሽ ወገን ነው” በሚል መሪህ ያለውን ችግር በስፍራው ደርሶ በማየት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ማለትም 300 የቤት ቆርቆሮ ፣ 200 ስፖንጅ ፍራሽ ፣ 150 የመመገቢያ ሰሀን ፣ 150 ባለ 20 ሊትር እና 100 ባለ 5 ሊትር የውሃ መቅጃ ጀርካን የተበረከተ መሆኑን ጭምር ገልፀዋል፡፡ 

በመጨረሻም ፕሬዝዳንቱ ለተፈናቃዮቹ “ብርታትና ፅናትን ፈጣሪ ይስጣችሁ! አይዞአችሁ! ሁሌም ከጎናችሁ ነን” በማለት መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡

  

Odoo • Image and Text

ሚያዝያ 25,2011 ዓ/ም

ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በውሽውሽ ቀበሌ በበካ መንደር በማር ምርት ለተሰማሩ ማህበራት 10 ዘመናዊ ቀፎ እና 5 የንብ ማጥመጃ ሳጥን በማበርከት የተግባር ስልጠና ሰጠ፡፡

በስልጠናውም መድረክ የማህበራቱ አባላት ዩኒቨርሲቲው ላበረከተላቸው ቁሳቁስና ለሰጠው የተግባር ስልጠና በማመስገን በቀጣይ ተጠናክረን በመስራት ለሌሎች አርአያ ሆነን የእኛን ፈለግ እንዲከተሉ በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው ራዕይ መሳካት የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ ሀሳባቸውን ገልፀዋል፡፡

Odoo • Image and Text

ሚያዝያ 25, 2011 ዓ/ም

ዩኒቨርሲቲው በማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ በአካባቢው ለሚገኝ ሮሆቦት መዋለ ህፃናት የመጽሐፍትና የፅህፈት መሣሪያ ድጋፍ አደረገ፡፡

በመድረኩም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት፣ ም/ፕሬዝዳንቶች፣ መካከለኛ አመራሮች፣ የሮሆቦት መዋለ ህጻናት ት/ቤት ባለቤት እና በዩኒቨርሲቲው ከ3.8 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱም በመክፈቻ ንግግራቸው በሀገር ደረጃ በአዲሱ የት/ት ፍኖተ ካርታ ላይ ተማሪዎችን ከሥር መሰረታቸው በዕውቀትና በሥነ-ምግባር ማነፅ ተገቢ እንደሆነና ይህ ካልሆነ ግን ወደ ላይኛው የት/ት እርከን ከፍ እያሉ ሲመጡ እንደሚቸገሩ በመግለፅ በትምህርት ተቋማት ላይ ኢንቨስት ማድረግ ለሀገር ቀጣይነት ዋስትና መሆኑን ገልፀዋል፡፡ 

በመሆኑም ዩኒቨርሲቲው በዞኑ ካሉ ወረዳዎች መካከል በአራት ወረዳዎች /ጌሻ፣ ሳይለም፣ ጠሎና ጨታ/ ለተከታታይ ሁለት ወራት መ/ራንን በመላክ የ10ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ት/ት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በዩኒቨርሲቲው ከ3.8 በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የመ/ራኖቻቸውን ፈለግ በመከተል በጊምቦ ወረዳና በቦንጋ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ አራት አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ የ7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ይህም ለአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች መነቃቃትን እንደሚፈጥርና ተማሪዎቹም ከተለያየ ክልልና ብሄር የመጡ እንደመሆናቸው መጠን ህብረ-ብሔራዊነትን ለማጠናከርና የአካባቢውን ማህበረሰብ ባህልና ወግ ብሎም አካባቢውን እንዲያውቁት ምቹ አጋጣሚ ነው በማለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ገልፀዋል፡፡       

በመቀጠልም ፕሬዝዳንቱ የዕለቱ እንግዳና የሮሆቦት ት/ቤት ባለቤት በሆኑት በአቶ ታምሩ አማዴ እና ጓደኛቸው የተከፈተው መዋለ ህፃናት በዩኒቨርሲቲው ቢደገፍ የራሳቸውን ልጆች በሙሉ አስተምረው ለከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ ባበቁት ልክ በአሁኑ ሰዓት በት/ቤታቸው የሚማሩ ህፃናቶችን ለቁም ነገር ያበቃሉ በሚል ሙሉ ዕምነት በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገ/ት ም/ፕሬዝዳንት አማካይነት የተለያየ ይዘት ያላቸውን የማስተማሪያ መፅሐፍትና የፅህፈት መሳሪያዎችን አበርክተዋል፡፡

በመጨረሻም አቶ ታምሩ አማዴ ልጆቻቸውን ለቁም ነገር ያበቁበትን የራሳቸውን የህይወት ተሞክሮ በመድረኩ ለተገኙ ሠራተኞችና ተማሪዎች በማካፈል ለተደረገላቸው ድጋፍ በት/ቤታቸውና በራሳቸው ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

Odoo • Image and Text

ሚያዝያ 07/2011 ዓ.ም

በትናንትናዉ ዕለት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ “ከኣካባቢ ቆሻሻን ከአዕምሮ ከፋትንና ጥላቻን በማፅዳት ሠላምና ልማቷ  ቀጣይ የሆነች ኢትዮጵያን ለቀጣይ ትውልድ እናስረክባለን!” በሚል መሪ ቃል በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የፅዳት ዘመቻ አደረገ፡፡

በዕለቱም ሁሌም ሰርቶ የማሰራት መሪህን ተግባራዊ የሚያደርጉ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንትና ም/ፕሬዚዳንቶች ከባልደረቦቻቸው ጋር አብረው እያፀዱ በማፀዳት የዕለቱን የፅዳት ዘመቻ የተሳካ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ 

በመጨረሻም ፕሬዚዳንቱ ሀገራዊና ተቋማዊ  ተልዕኮአቸውን ለመወጣት በዘመቻው ላይ ለተሳተፉ ሁሉ ላቅ ያለ ምሰጋናቸውን በማቅረብ በቀጣይም ይህንኑ ተግባር ከዚህ ቀደም እኛ ‘’የሰፈር ቆሻሻን በእጃችን የአስተሳሰብ ቆሻሻን በብዕራችን’’ በሚል መሪ ቃል በወር አንድ ጊዜ የጀመርነውን የፅዳት ዘመቻ አጠናክረን በመቀጠል ዩኒቨርሲቲያችንን ለግቢው ማህበረሰብም ሆነ ከውጭ ለሚመጡ እንግዶቻችን ፅዱ ምቹና ማራኪ በማድረግ ግንባር ቀደምና ተናፋቂ ማድረግ አለብን በማለት አሳስበዋል፡፡