
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በዛሬው ዕለት የተማሪዎች ዕውቅና ፣ የአረጋውያን ማዕከል እና የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያ FM. 92.1ጣቢያ ሥራ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር አከናወነ፡፡
ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም.*
መድረኩ በአባቶች ምረቃ የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል የቦንጋ ዩኒቨረሲቲ ፕሬዝዳንት ደጋለ ኤርገኖ (ዶ/ር) ባደረጉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እያከናወነ ያለውን የመማር ማስተማር፣ የምርምር ፣እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ተጋባራት ዙሪያ ሰፊ የሆነ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን. . .
ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች መልካም ምኞታቸውንም የገለጹት ፕሬዘዳንቱ በተለይ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና ሰራተኞች ከደመወዛቸው በፈቃዳቸው መቁረጣቸውን አሞግሰው የማህበረሰብ አገልግሎትን በዘመነና በተሻለ ጥራት ለማድረስ ዛሬ የሚመረቀው የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያም ምቹ መደላድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
የተማሪዎች ዕውቅናና ሽልማት ቀጥሎ የተከናወነ ሲሆን በክቡር አቶ አልማው ዘውዴ መሪነት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአስ/ር ቦርድ አባላት እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ በመሆን ሽልማቱን ለተማሪዎች አበርክተዋል፡፡













በመቀጠል በክቡር አቶ አልማው ዘውዴ መሰረታዊ የሆነ ቁልፍ መልእክት የተላለፈ ሲሆን በተለይ በቀድሞ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የተጀመሩ መልካም ተግበራት መቀጠላቸው ተቋማዊ ግንባታው በመልካም መሰረት ላይ የታነጸ ለመሆኑ ማሳያ እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
የት/ት ስብራትን ለመጠገን እየሰራ ያለውን ስራ እውቅና የሚሰጡ መሆኑን ገልጸው በተለይ ተማሪዎችን የማበረታታቱ ተግባር ሎሎች ተማሪዎችንም የሚያነቃቃ እና የሚደነቅ ተግባር እንደሆነ አስገንዝበዋል፡፡
በተለይ እንደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ከተማሪዎች ውጤት አንጻር የታየውን አንጻራዊ ለውጥ አውስተው በቀጣይም የክልሉን የመምህራን አቅም ለማሻሻል ከዩኒቨርሲቲው ጋር አብሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ሬድዮ እና የአረጋውያን ስራ ማስጀመሪያ መርሀ-ግበር ሌላው የዛሬው ግዙፍ ኩነት ሲሆን የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ አልማው ዘውዴ መሪነት ፣የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አስ/ር ቦርድ አባላት፣ የፋና ሚዲያ ኮርፖሬት ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት በተገኙበት የሪቫን ቆረጣ እና የስቲዲዮ ጉብኝት ተደርጓል፡፡
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) በይፋ የማህበረሰብ ሬድዮ ጣቢያው FM. 92.1 መመረቁን የሚበስር መልዕክት በሬድዮ ጣቢያው ቀጥታ ስርጭት አስተላልፈዋል፡፡
የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል ስራ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ሌላው ግዙፍ ኩነት ሲሆን ስለ ማዕከሉ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ተረፈ ሀ/ማሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በጋራ እንችላለን!
