Back

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከት/ት ሚኒስቴር ጋር የKPI ተግባራትን አስመልክቶ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

*****መስከረም 30/2018 ዓ.ም*****

የቁልፍ ተግባር አመልካች / Key Performance Indicators – KPI / ከባለፈው 2017 ዓ.ም ጀምሮ ት/ት ሚኒስቴር ከፍተኛ ት/ት ተቋማትን ተግባር ለመመዘን ተግባር ላይ የዋለ ሲሆን ተቋማትም ተልዕኳቸውን ከ KPI አንጻር እየፈተሹ የሚተገብሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚሁ መሰረት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አስተደደር ቦርድ ሰብሳቢ አፉወርቅ ካሱ (ፕ/ር) እና የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ከክቡር ሚ/ር ኮራ ጡሹኔ ጋር ተፈራርመዋል፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የት/ት ሚኒስቴር ሚኒስትር ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በተለይ ስለ ከፍተኛ ት/ት ማሻሻያ ፕሮግራሞች፣ መረጃ አያያዝ ፣ የተቋማት ልየታ እና የፕሮግራች የዕውቅና አሰጣጥ ሂደት ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል በተጨማሪም ወደፊት ምንም ዓይነት የተማሪዎች ምደባ እንደማይኖር እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉት ዩኒቨርሲቲ በቀጥታ ማመልከት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ቦርድ አባላትን ጨምሮ የት/ት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በጋራ እንችላለን!