
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ ።
** *መስከረም 23 /2018 ዓ.ም****
“ኢሬቻ የአብሮነት፣የአንድነትና የወንድማማችነት ተምሳሌት ሆኖ ለዘመናት የዘለቀ የሰፊው የኦሮሞ ህዝብ ውብ ባህላዊ እሴት ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ . . .
እኛ ኢትዮጵያውያን የብዝሀነትና የረጅም ታሪክ ባለቤት መሆናችን ማሳያ የሆነው የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት ከሚከውናቸው ዋና የባህል ኩነት ቀዳሚው ነው፡፡ የኦሮሞም ህዝብ ከአብሮነት እሴቱ ባሻገር ፈጣሪን ስላለፈው የክረምት እና የዝመራ ወቅት በማመስገን መጪውን ብርሃን በተስፋ እንዲሁም ለፈጣሪ ምስጋናን በማቅረብ የሚጀመርበት ትልቅ ባህላዊና ህዝባዊ ትዕይንት ነው፡፡
በመሆኑም ዩኒቨርሲቲያችንም ለዚህ ግዙፍ እና ቱባ ባህል ባለቤት ለሆነው የኦሮሞ ወንድም ህዝብ በዓሉን አስመልክቶ መልካም ምኞታችንን ስንገልጽ ከልብ የተሰማንን ኢትዮጵያዊ ወንድማማችነትን እና አብሮነታችንን ከማሳየትም ባሻገር በዓሉ የሰላም ߹የጤና ߹የብልጽግና እንዲሁም የተሸለ አብሮነት የሚጎለብትበት እንዲሆን በመመኘት ነው፡፡
በድጋሚ እንኳን አደረሳችሁ፣ አደረሰን መልካም የኢሬቻ በዓል !
ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር)
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት!
