*ሰኔ 14/2017 ዓ.ምመርሀ-ግብሩ በአባቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የቦርድ አመራሮችን እንዲሁም የዕለቱን የክብር እንግዳ እና ከተለያዩ መዋቅር የተጋበዙ አካላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ነበር። በመልዕክታቸው የዩኒቨርስቲው በመማር መስተማር ߹በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት እየሰራ ያለውን የተለያዩ ተግባራት አብራርተዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ማስረሻ በላቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ ባስተላለፉት መልእክት የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት ምዕራፍ ያላቸው በቂ የተማረ የሰው ሀይል መሆኑን ገልጸው መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም አውስተዋል። የትምህርት ዘመን የሚጠናቀቅ ሳይሆን የሚቀጥል በመሆኑ የዛሬ ምሩቃንም …