Back
09 July

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ዘርፍ ያስተማራቸውን  918 ተማሪዎችን ለ6ኛ ጊዜ አስመረቀ።

                  *ሰኔ 14/2017 ዓ.ምመርሀ-ግብሩ በአባቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት  የተጀመረ ሲሆን በመቀጠል የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የቦርድ አመራሮችን እንዲሁም የዕለቱን የክብር እንግዳ እና ከተለያዩ መዋቅር የተጋበዙ አካላትን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ነበር። በመልዕክታቸው የዩኒቨርስቲው በመማር መስተማር ߹በጥናትና ምርምር እንዲሁም በማህበረሰብ አገልግሎት እየሰራ  ያለውን የተለያዩ ተግባራት አብራርተዋል። የዕለቱ የክብር እንግዳ  ክቡር አቶ ማስረሻ በላቸው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሀላፊ ባስተላለፉት መልእክት የበለጸጉ ሀገራት ዛሬ ለደረሱበት ምዕራፍ ያላቸው በቂ የተማረ የሰው ሀይል መሆኑን ገልጸው መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መሆኑንም አውስተዋል። የትምህርት ዘመን የሚጠናቀቅ ሳይሆን የሚቀጥል በመሆኑ የዛሬ ምሩቃንም …

20 January

The Minister of Education of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, Prof. Berhanu Nega, spoke to the Bonga University Community.

መጋቢት 11/2014 ዓ.ም   የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ዉይይት አደረጉ፤  የዉይይቱን መድረክ የከፈቱት  የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጰጥሮስ ወ/ጊዮርጊስ የዉይይቱ ማስጀመሪያ  እና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዉ  አጠቃላይ ስለ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ዋና ዋና እንቅስቃሴዎች የሚያስቃኝ ሰነድ ለተሳታፊዎች አቅርበዋሉ፡፡  ዉይይቱ  የሀገርቱን የትምህርት ሥርዓት በጋራ ዕይታ እና መግባባት መምራት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ያለመ ነዉ፡፡  የትምህርት ሥርዓቱ ዙሪያ ያሉ ችግሮች ዙሪያ የዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ጥያቄዎችን አንስተዉ በትምህርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፈሰር ብርሃኑ ነጋ፤በከፍተኛ ትምህርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ እና በትምህርት  ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ፋንታ ማንደፍሮ  ምላሽእና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡  ሚኒስቴሩ አክለዉም የትምህርት …