
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ገለፃ/Orientation /ሰጠ።
ሰኔ 30/2017ዓ.ም
መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ነበር የከፈቱት።
አክለውም ተማሪዎችን ያበረታቱ ሲሆን ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባቸው በመግለጽ መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።



የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዓቀፍ ፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ ደሱ ለተፈታኞች አጠቃላይ የሆነ ከፈተናው ጋር የተያያዙ መሠረታዊ ነጥቦችን በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመድረኩ ላይ የተማሪዎች ዲን ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ የሁሉም ሚና የተብራራበት ሲሆን ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውም ተበራርቷል።
በጋራ እንችላለን!