Back
09 July

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ገለፃ/Orientation /ሰጠ።

ሰኔ 30/2017ዓ.ም መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ነበር የከፈቱት። አክለውም ተማሪዎችን ያበረታቱ ሲሆን ፈተናውን በተረጋጋ መንፈስ በመስራት የተሻለ ውጤት ማምጣት እንደሚገባቸው በመግለጽ መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዓቀፍ ፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ ደሱ ለተፈታኞች አጠቃላይ የሆነ ከፈተናው ጋር የተያያዙ መሠረታዊ ነጥቦችን በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ የተማሪዎች ዲን ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ የሁሉም ሚና የተብራራበት ሲሆን ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውም ተበራርቷል። በጋራ እንችላለን!

09 July

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀመሩ።

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም. ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የት/ት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢንጂነር) ጋር በመሆን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀምረዋል። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር)በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ት/ት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የፌደራል የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ሚኒስትሩንና ልኡካቸውን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ለተፈታኞች ባስተላለፉት መልእክት እናንተን የመጣል ፍላጎት ስላለን ሳይሆን …

09 July

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ለ2017ዓ.ም 12ኛ ክፍል ለመጀመሪያ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ገለፃ /Orientation /ተሰጠ።

ሰኔ 22/2017ዓ.ም መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካ/ምር/ቴክ/ሽግግርና ማህበረሰብ አ/ት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ (ዶ/ር) ተማሪዎችን እንኳን ወደ ቤታችሁ በሰላም መጣችሁ በማለት ነበር። የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የሀገር ዓቀፍ ፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ ደሱ ለተፈታኞች አጠቃላይ የሆነ ከፈተናው ጋር የተያያዙ መሠረታዊ ነጥቦችን በማንሳት ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመድረኩ ላይ የተማሪዎች ዲን የፌደራል ፖሊስ አባላት እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተገኙ ሲሆን ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ የሁንሉም ሚና ከማብራራት ባሻገር ተማሪዎች በተረጋጋ ሁኔታ ፈተናውን መስራት እንደሚገባቸው በአጽንኦት ተገልጿል። በጋራ እንችላለን!

09 July

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሰኔ 20/2017 ዓ.ም በነገዉ ዕለት በካፋ ዞን ከሚገኙ 17ቱም መዋቅሮች 60 2ኛ ት/ቤቶች የተመደቡለትን 2240 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቀበል እንደሚጀምር አስታውቀዋል። ፈተናዉ ከኩረጃና ተያያዥ ከሆኑ ማጭበርበሮች በጸዳ መልኩ እንዲከናወን ተማሪዎቻችን በራስ መተማመን አጎልብተዉና ተረጋግተዉ ፈተናዉን እንዲወስዱ ዩኒቨርስቲዉ የሚቻለዉን ሁሉ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል። በድጋሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸዉ እመኛለሁ። ደጋላ ኤርገኖ (ዶ/ር)ፕሬዝዳንት

09 July

ለ2017ዓ.ም.ሀገራዊው የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ስላለው ቅድመ ዝግጅት ከተለያዩ ከውስጥና ውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።

ሰኔ 19/2017ዓ.ም***, መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ(ዶ/ር) ከት/ት ምኒስቴር ተወክለው የመጡ የፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ     በጋራ በመሆን ነበር ወይይቱን የመሩት። በውይይቱ የዘንድሮውን ፈተና ለማከናወን ያሉ አስቻይ ሁኔታዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ክፍሎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። የተማሪዎች አገልግሎት: የፋይናንስ: የፈተና ክፍል ዝግጅት :የትራንስፖርትና ስምሪት :  እንዲሁም የፀጥታ ሀይሉ በዋናነት ማብራሪያ የሠጡ አካላት ናቸው። የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎችም የተነሱ ሲሆን የሚመለከታየው አካላትም ምላሽ ሰጥተዋል። ለዘንድሮ ፈተና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 5631 ተማሪዎች ሲሆኑ ከሰኔ 21/2017 ዓ.ም.ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ ሰኔ 22/2017ዓ.ም ስለ …