Back

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀመሩ።

ሰኔ 23/2017 ዓ.ም.

ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የት/ት ሚኒስቴር ሚኒስትር ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ኢንጂነር) ጋር በመሆን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በመገኘት ሀገር ዓቀፉን የ12ኛ ክፍል ፈተና አስጀምረዋል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር)በምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ት/ት ቢሮ ሀላፊ አቶ አልማው ዘውዴ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንቶች እንዲሁም ሌሎች የፌደራል የክልል እና የዞን ከፍተኛ አመራሮች በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ሚኒስትሩንና ልኡካቸውን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን

ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ለተፈታኞች ባስተላለፉት መልእክት እናንተን የመጣል ፍላጎት ስላለን ሳይሆን ጠንካራና በራሱ የሚተማመን ተማሪ ለማፍራት ካለን ጽኑ ፍላጎት ነው የፈተና ስርዓቱን በዚህ መልክ ያደረግነው ብለዋል።

ተማሪዎችን በማበረታታት መልካም ምኞታቸውንም አስተላልፈዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልላዊ መንግስት ርዕሰ-መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር ) በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ክቡር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ ወደ ክልላችን መጥተው ይሄንን የ12ኛ ክፍል ሀገር ዓቀፍ ፈተና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ስላስጀመሩ እና ተማሪዎችን ስላበረታቱ አመስግነዋል።

ይሄ ለተማሪዎቻችን ትልቅ ዕድልም አቅምም ነው ሚፈጥረው ያሉት ርዕሰ-መስተዳድሩ ተማሪዎች ተረጋግተው መስራት እንደሚገባቸው ምክራቸውን በመለገስ መልካም ምኞታቸውን ለተማሪዎች አስተላልፈዋል።

በጋራ እችላለን!