Back

ለ2017ዓ.ም.ሀገራዊው የ12ኛ ክፍል ፈተናን በተመለከተ ስላለው ቅድመ ዝግጅት ከተለያዩ ከውስጥና ውጭ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።

ሰኔ 19/2017ዓ.ም***,

መድረኩን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምርምር የቴክኖሎጂ ሽግግር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ከለለው አዲሱ(ዶ/ር) ከት/ት ምኒስቴር ተወክለው የመጡ የፈተና ጣቢያ ሀላፊ አቶ ደጀኔ     በጋራ በመሆን ነበር ወይይቱን የመሩት።

በውይይቱ የዘንድሮውን ፈተና ለማከናወን ያሉ አስቻይ ሁኔታዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርሲቲው የተለያዩ የስራ ክፍሎች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።

የተማሪዎች አገልግሎት: የፋይናንስ: የፈተና ክፍል ዝግጅት :የትራንስፖርትና ስምሪት :  እንዲሁም የፀጥታ ሀይሉ በዋናነት ማብራሪያ የሠጡ አካላት ናቸው።

የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎችም የተነሱ ሲሆን የሚመለከታየው አካላትም ምላሽ ሰጥተዋል።

ለዘንድሮ ፈተና በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፈተናውን የሚወስዱ ተማሪዎች በተፈጥሮ ሳይንስ እና በማህበራዊ ሳይንስ በአጠቃላይ 5631 ተማሪዎች ሲሆኑ ከሰኔ 21/2017 ዓ.ም.ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ ሰኔ 22/2017ዓ.ም ስለ ፈተናው ገለፃ /Orientation / እንደሚሰጣቸው ተገልጿል።

የፈተና ጣቢያው   ፎካል ፐርሰን ያሬድ አያሌው (ዶ/ር) በመጨረሻ ባስተላለፉት መልእክት ፈተናውን የተሳካ ለማድረግ እዚህ የተሰበሰበው ግብረ-ሀይል ከማንም በላይ ሀላፊነት ስላለበት የተጣለብንን ይሄንን ሀገራዊ ሀላፊነት እስኪጠናቀቅ ድረስ የበኩላችንን እንድናደረግ በማለት አሳስበዋል።

በጋራ እንችላለን!