Back

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠዉን የ12ኛ ክፍል ፈተና ለመስጠት ዝግጅቱን ያጠናቀቀ መሆኑን የዩኒቨርስቲው ፕሬዚደንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

ሰኔ 20/2017 ዓ.ም

በነገዉ ዕለት በካፋ ዞን ከሚገኙ 17ቱም መዋቅሮች 60 2ኛ ት/ቤቶች የተመደቡለትን 2240 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መቀበል እንደሚጀምር አስታውቀዋል።

ፈተናዉ ከኩረጃና ተያያዥ ከሆኑ ማጭበርበሮች በጸዳ መልኩ እንዲከናወን ተማሪዎቻችን በራስ መተማመን አጎልብተዉና ተረጋግተዉ ፈተናዉን እንዲወስዱ ዩኒቨርስቲዉ የሚቻለዉን ሁሉ እንደሚያደርግ አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።

በድጋሚ ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም እድል እንዲገጥማቸዉ እመኛለሁ።

ደጋላ ኤርገኖ (ዶ/ር)
ፕሬዝዳንት

    በጋራ እንችላለን!