Bonga University

Latest News & Updates

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የትንሳኤ በዓል መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የትንሳኤ በዓል መልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላለፉ።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ ዶ/ር) የበዓል መልካም ምኞት መግለጫቸውን ባስተላለፉበት ወቅት እንደጠቀሱት የፋሲካ በዓል ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም ሕዝብ ሀጢያት የከፈለው የደም ዋጋ ውጤት መሆኑን ገልፀዋል።


ክቡር ፕሬዝዳንቱ መልእክታቸውን ቀጥለው  በትንሳኤ የዓለም ፈጣሪ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ሀጢያተኛ ለሆንነው  ለእኛ ለሰው ልጆች ያለውን  ጥልቅ ፍቅር ገልጿል።
ለተከፈለልን የህይወት እና ንፁህ ደም ዋጋ እኛም ከተደረገልን ጋር ባይወዳደርም የተቸገሩትን ከማሰብ ባሻገር ማዕድ በማጋራት ፍቅራችንን በተግባር በመግለጽ በዓሉን ማክበር  እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተው ገልፀዋል።


በመጨረሻም ለመላው የዩኒቨርሲቲያችን የክርስትና እምነት ተከታዮች እንዲሁም በዓሉን ለሚያከብሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ ያሉ ሲሆን. . .በዓሉ የሰላም ፣ የጤና ፣ የፍቅር እንዲሁም የመተሳሰብ እንዲሆን ምኞታቸውን በመግለጽ የበዓል መልካም ምኞት መልዕክታቸውን  አጠቃልለዋል።



መልካም የትንሳኤ በዓል!!
ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት!
በጋራ እንችላለን!

Back to News