ሪፖርቱን የዩኒቨርሲቲው ስትራተጂክ ጉዳዮች ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አማረ ወ/ገብርኤል ቀርቧል።
ሪፖርቱ በመማር ማስተማር ፣ በምርምር ፣ በማህበረሰብ አገ/ት እና መሠል ሌሎች ተግባራት ላይ የተሰሩ ተግባራት በዝርዝር ቀርቧል።
በተጨማሪም የ2019 ዓ.ም መነሻ ጠቋሚ ዕቅድ የዩኒቨርሲቲውን ግብ እና ቁልፍ ተግባር አመልካች /KPI / መሠረት አድርጎ ቀርቧል።
ሪፖርቱ እና ጠቋሚ ዕቅዱ ከቀረበ በኋላ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ከምክትል ፕሬዝደንቶች እና የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ ጋር በመሆን በቀረበው ሪፖርት እና ዕቅድ ላይ ማብራሪያ በመስጠት ለውውይት መድረኩን ከፍተዋል።
ያሳካናቸውን በማጠናከር የታዩ ክፍተቶችን መሙላት እንደሚያስፈልግ በምክትል ፕሬዝዳንቶቹ እና በፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተዘርዝሮ ቀርቧል።
የካውንስል አባላትም በርከት ያሉ የተለያዩ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን አንስተዋል።
ለተነሱ ጥያቄዎችም የሚመለከታቸው አካላት ተገቢ ምላሽ የሰጡ ሲሆን እንደግብዓት የተወስዱ ሪፖርት እና ዕቅዱን የሚያጎለብቱም ነጥቦችም ነበሩ።
በመጨረሻም ክቡር ፕሬዝዳንቱ በሰጡት ማጠቃለያ ለካውንስሉ አባላት ንቁ ተሳትፎ አመስግነው የተነሱ ነጥቦችን መሠረት አድርገው ሰፊ የሆነ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተለይ ዕቅዱ ያለቀለት ባለመሆኑ የተነሱ ሀሳቦች እንደሚካተቱ ገልፀው በቀጣይ 2019 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ ጠንክሮ መስራት ይገባል ብለዋል።
ክቡር ፕሬዝዳንቱ ትኩረት ከሰጧቸው ነጥቦች መካከል KPI ፣ የተቋም ህልውና፣ የራስ - ገዝ ጉዞ፣ የተቋም ማሻሻያ ፣ ዓለም ዓቀፍ ትብብሮች እና የተቀናጁ የምርምር ተግባራት ፣ ሀብት ማመንጨት ፣ በቡና ሳይንስ ልቆ መውጣት ፣የቴክኖሎጂ መሠረተ-ልማት ማስፋፋት እና የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ማጠናከር ላይ መሠረት በማድረግ ተግባራቶቻችንን በመፈፀም በመጪው 2019 ዓ.ም የተሻለ አፈፃፀም ለማስመዝገብ የበኩላችንን ማድረግ ይገባናል በማለት ሪፖርት እና ዕቅዱን በማፅደቅ የዕለቱ መርሀ-ግብር ተቋጭቷል።