ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት መርሀ-ግብር ከሐምሌ 4/2018 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ተግባራት ሲከናወን ቆይቶ ዛሬ ተጠናቋል።
በዛሬው የመጨረሻ ቀን መርሀ-ግብር የአንዲት በጥልቅ ድህነት ውስጥ ያለች ሴት የስምንት ልጆች እናት በቦንጋ ከተማ ልዩ ስሙ በሚሽን ሰፈር አካባቢ የቤት እድሳት መርሀ-ግብር በማስጀመር ነበር።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) በመርሀ -ግብሩ ማስጀመሪያ ወቅት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ክቡር ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ከሚያከናውናቸው ዘርፈ ብዙ ተግባራት አንዱ እንደነዚህ አይነት የማህበረሰብ አገልግሎት እና ሰብዓዊ ድጋፍ መሆኑን ጠቅሰው ዛሬ ቤት የምናድስላት ሴት ደግሞ እጅግ በጣም ችግረኛ በመሆኗ እኛም የአቅማችንን በማድረግ ሀገራዊ ሀላፊነታችንን ለመወጣት ያስችለናል ብለዋል በዚህም ደስተኞች ነን ብለዋል።
በክቡር ፕሬዝዳንቱ መሪነትም የቤት እድሳቱ የግንባታውን ሂደት በይፋ በማስጀመር ወደ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ አረጋውያን ማዕከል ችግኝ ተከላ ፕሮግራም መካሄድ ችሏል።
በአረጋውያን ማዕከል በተከናወነው ፕሮግራም የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ አካቶ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አልማዝ ሀ/ወልድ የማዕከሉን የስራ እንቅስቃሴ የሚገልጽ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል።
በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ መርሀ-ግብር ማጠቃለያ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) ቀርቧል።
በመልዕክታቸውም ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስ/ር ሰራተኞችን ለማዕከሉ ለሚያደርጉት ድጋፍ አመስግነው እንደዚህ አይነት ሰብዓዊ ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ለማዕከሉ አረጋውያን ረጅምን ዕድሜ ተመኝተዋል።
ክቡር ፕሬዝዳንቱ የተለያዩ የመንግስት መዋቅሮችን ያመሠገኑ ሲሆን በማጠቃለያው ለአረጋውያኑ ድጋፍ የአልባሳት ፣ የገንዘብ እና የቴምር ድጋፍ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) የተላኩትን ስጦታዎች ለአረጋውያኑ በማበርከት የፕሮግራም ፍፃሜ ሆኗል።
በጋራ እንችላለን!