ከቦንጋ ከተማ ወደ አረጋውያን ማዕከሉ በ2017 ዓ.ም የገቡት እኚህ አባት ስማቸው አቶ ጌታቸው ገ/ፃዲቅ ይባላሉ።
ምንም ረዳትም ሆነ ጧሪ የሌላቸው እኚህ አባት በቦንጋ ዩኒቨረርሲቲ የአረጋውያን እንክብካቤ ማዕከል በልዩ እንክብካቤ ኖረዋል።
ባገጠማቸው ተደጋጋሚ የጤና እክል በማዕከሉ የጤና ባለሙያዎች ድጋፍ እና እንክብካቤ ሲደረግላቸው ቆይቶ በተወለዱ በ75 ዓመታቸው ነሀሴ 15/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 2:ዐዐ ሰዓት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) እንዲሁም ምክትል ፕሬዝዳንቶች ፣ የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ሀላፊ ፣ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ፣ ሠምህራንና አስ/ር ሰራተኞች እንዲሁም የአካባቢ ነዋሪዎች በተገኙበት በተክለኃይማኖት ቤተ-ክርስቲያን ስርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል።
አቶ ጌታቸው ገ/ፃዲቅ ተግባቢ እና ንቁ አባት ነበሩ።
ነፍሳቸው በሰላም ትረፍ!!
ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ!
በጋራ እንችላለን!