የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትም/ት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ መ/ራንን እያወያዩ ይገኛሉ።
ክቡር ሚኒስትሩ የተማሪዎችን ካፍቴሪያ በመጎብኘት የጀመሩ ሲሆን በመቀጠል የዩኒቨርሲቲውን መምህራን እና የተማሪዎች ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
ክቡር ሚንስትሩ በገለፃቸው በተለይ ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት 25 ዓመታት ልትደርስበት ስለታለመው ትልቅ የቴክኖሎጂ ብሎም የሁለንተናዊ ዕድገት ከፍታ አብራርተዋል።
ዩኒቨርሲቲዎች በዓለም ዓቀፍ እይታ ፣ በሀሳብ ገበያ ፣ በጥናትና ምርምር እንዲሁም የዩኒቨርሲቲዎች ማሻሻያ/Reforms/ ዙሪያ መታወቅ ስለሚገቧቸው ነጥቦች ዙሪያ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ከመ/ራን እና ከተማሪዎችም ከመ/ራን ጥቅማጥቅም ፣ ከትኩረት መስክ ልየታ፣ስለመውጫ ፈተና ፣ ስለዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች አሰያየም እና መሠል ጥያቄዎች ተነስተዋል።
ክቡር ሚኒስትሩም ለተነሱ ጥያቄዎች ተገቢውን ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ ሀገራችን የሁላችንም እንደሆነች በማሰብ በዕውቀትም በቴክኖሎጂም የተሻለች እንድትሆን ጠንክሮ መስራት እንደሚገባ በማሳሰብ ውይይቱ ተቋጭቷል።
በጋራ እንችላለን!